Followers (0)  Read (0)  Reviewed (1)   Rated (1)
Yeabtsega Ambaw reviewed   ደስታን ፍለጋ by የአብፀጋ አምባው
    ስለመፅሐፉ ማብራርያ ለመስጠት ያህል መፅሐፉ ሲነበብ ዶፓሚን፤ ሴሮቶኒን፣ ኦክሳሳይቶሲንና ኢንዶርፊን የተባሉ ኬሚካሎች እንዲለቀቁ በረቀቀ መንገድ ነው ያዘጋጀሁት። በመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች ዶፓሚንን ሲያነሳሳ ቀጥሎ ባሉት ምዕራፎች እውነተኛ ደስታ ማለትም ሴሮቶኒን እንዲለቀቅ አድርጌያለሁ። መፅሐፉ ሲነበብ ሰውነታችን የደስታ ሆርሞኖችን እንዲያመነጭ በሚያደርግ መልኩ የራሴን የስነ-ፅሑፍ ፎርሙላ ተጠቅሜያለሁ። የመፅሐፉ የመጀመሪያ ምዕራፎች እንደመንደርደሪያ ሲሆኑ የታሪኩ ምርጥ ክፍል ቀጥሎ ባሉት ምዕራፎች ይገኛል። መፅሐፉ ውስጥ በልጅነት ስንዘምራቸው የነበርናቸው የልጅነት መዝሙሮች ውስጥ ያሉ ፍጡሮችና ትዕይንቶች ተካተውበታል። ለምሳሌ ብስኩት አደባባይ ፤ መሀሉ ላይ ትልቅ የጉንዳን ሐውልት ያለው በብስኩት፣ በጀላቲ በአይስክሬም የተከበበ አደባባይ ይገኛል። አደባባዩ አጠገብ ሁለት ዛፎች አሉ ። ዛፎቹ የሚስጥራዊው ዓለም በሮች ናቸው። በሚስጥራዊው ዓለም በዓይነታቸው ልዩ የሆኑ ፍጥረታትን እናገኛለን። ወንድ የሚባል ዘር አይተው የማያውቁ ድንግል ልዕልቶች፤ ዘላለም የሚኖሩ ዘጠኝ እህትማማቾች ፤ ዘላለማዊነትን የሚመልሰው መረቅ፤ የሚራመድ እሾሃማ ሀረግ ፤ አኒሞን የተባሉ ሰው በል የዕፅዋት ዘሮች ወረራ፤ ክንፍ ያላት አረንጓዴ አንበሳ.... ወዘተ የሚስጥራዊው ዓለም ነዋሪዋች ናቸው። የአካል ስነ መዋቅር ፤ ሆርሞኖች ገፀ ባህሪ ሆኖው ይናገራሉ። የደስታን ትርጉም በድርሰቱ ውስጥ ለመግለፅ ሞክሬያለሁ። መፅሐፉን በማንበብ ከታሪኮቹ ፍሰትም የደስታ ሆርሞኖች እንዲነቃቁ ለማድረግ ሞክሬያለሁ። ለዚህም የህክምና ተማሪ መሆኔ ጠቅሞኛል ብዬ አስባለሁ።