Solomon Getnet

Followers (0)  Read (0)  Reviewed (3)   Rated (0)


Recent Activities


Solomon Getnet reviewed   የተጠላው እንዳልተጠላ by አለማየሁ ገላጋይ

    ታትሞ በቅርቡ ገበያ ላይ የዋለው የዓለማየሁ ገላጋይ “የተጠላው እንዳልተጠላ” መጽሃፍ አነበብኩት፡፡ ለጊዜው ማን ነው የተጠላ? ጠይውስ ማን ነው? የሚለውን ልተወው፡፡ በመጽሃፉ ውስጥ የእኔን እና መሰሎቼን የህይወት መሰረት የሆኑትን እሴቶች፤ እምነት፣ ባህልና ኢትዮጵያዊነት በዜሮ ነው ያባዛው፡፡ ማህበርና እድርም አልቀረው! አሌክስ ኢትዮጵያ አሁን ለምትገኝበት ዝቅጠት መሰረቱ ስንፍና ሲሆን ስንፍናው የሚመነጨው ደግሞ ከእምነታች፣ ከባህላችንና ለኢትዮጵያዊነት ከምንሰጠው ክፍ ያለ አመለካከት መሆኑን ይሞግታል፡፡ የኢትዮጵያ የሆነውን ሁሉ በጅምላ አውግዟል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ሰለጠኑ የሚባሉ ሀገሮች ባህልም ለኢትዮጵያ እንደማይሆን ተንትኗል፡፡ አሌክስ እድገትንና ለውጥን የተመለከተው ንዋይን ከመከማቸት ጋር ብቻ ነው ፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለንዋይ እንዲሰግድ ይመክራል፡፡ እኔ ግን እጠይቃለሁ፤ የሀገሩን እሴት የሁኑትን ሙሉ በሙሉ አውልቆ ጥሎ ያደገ ሀገር ከወዴት ይገኛል? እያንዳንዳችን ለህይወት ያለን ፍልስፍናን እነደምን አንድ ሆኖ ለንዋይ እንስገድ? ለዚህም የደራሲውን አሌክስ ህይወት መመልከት በቂ ይመስለኛል፡፡ ምናልባት አልክስ ይህንንም ስንፍናዬ ነው ካላለን፡፡ ምንም እንኳ ከሀይማኖታዊ አስተምሮ ውጭ የሆኑ ባህሎች ከእምነታችን ጋር የተቃላቁ እንዳሉ ባውቅም ሀይማትን የተቸበት አመክንዮዎች ደካማ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡ በሀገራችን ማህበራዊ አቢዎት መምጣት እንዳለበት ከሚያምኑ ሰዎች አንዱ ነኝ፡፡ ነገር ግን በዚህ መጽሃፍ ላይ በቀረበው መልኩ ከሆነ ግን ምናልባትም የከፋ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ብዙ እንዳነበበና የመጻፍ ልምድ እንዳለው ደራሲ አሌክስ ከዚህ በተሸለ ማቅረብ ይችል ነበር፡፡ መልካም ንባብ!


Solomon Getnet reviewed   በረራ ቀዳሚት አዲስ አበባ by ሀብታሙ መንግስቴ ተገኝ

    የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያን ታሪክ ለመረዳት በፕሮፌሰር ሀብታሙ ተገኘ የተሰናዳውን ''በራራ-ቀዳሚት አዲስ አበባ'' የተሰኘውን መጽሃፍ ማንበብ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የተቀዳው የተዛባ ታሪክን መሰረት አድርጎ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህ መጽሃፍ ቀዳሚ የጽሁፍ ማጣቀሻዎች የያዘ በመሆኑ ኢትዮጵያ አሁን ከምትገኝበት ችግር ለማላቀቅ ብቸኛው አማራጭ እውነተኛውን የኢትዮይያ ታሪክ በመነጋገርና ለዚሁም ፖለቲካዊ መፍትሄ በማፈላለግ ብቻ ይሆናል፡፡ ይንን መጽሃፍ ሳነብ ምናልባትም የዛሬ 500 ዓመት አገርን መልሶ የማቅናቱ ሂደት ለምን እንዳልተሳካ በምሁራን ከሚጠቀሱት አራት ምክንያቶች ሶስቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሆኑ መስለውኛል፡፡ 1. ኢትዮጵያ በግራኝ አህመድ ወረራ የተዳከመችበት ወቅት አማራውን ለስድሳ አመታት አገር አልባ አድረጎ በማሳደድ እንዲዳከም ከማድረግ ጋር፣ 2. በወቅቱ የነበሩ የነገስታት እቅም ማነስ ከተላላኪውና እና ሆድ አደሩ ብአዴን ጋር እንዲሁም 3. በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት አሁን ህወሃት ከከፈተው ጦርነት ጋር ተመሳስሎብኛል፡፡፡ እነዚህ ሶስት ምክንያቶች ባጋጣሚ ይሆን የተመሳሰሉት ወይስ ተጠንቶና ታቅዶ የተተገበሩ???


Solomon Getnet reviewed   ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ by ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቃውንት የክርስትና እምነት ወደ ኢትዮጵያ በኃዋርያት ዘመን በሶስት መንገዶች እንደመጣ ያስተምራሉ፡፡ እነዚህም 1. ግእዝ የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን በባእለ ጴንጤ ቆስጤን መሳተፋቸው 2. ኃዋርያው ማቴዎስ በኢትዮጵያ ወንጌልን መስበኩ እና 3. የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በዲያቆኑ ፊሊጶስ እጅ መጠመቁ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነውን የጃንደረባውን ማንነት ለማሣየት ጥናት በማድረግ ይህንን ‘’ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ’’ የተባል ድንቅ መጽሀፍ አበርክቶልናል፡፡ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ይህንን መጽሃፍ ሲጽፍ እኔ እንደተረዳሁት ሳይንሳዊ መንገድን በመከተል በቻለው መጠን የሚነሱ ሁሉን ጥያቄዎች በማየት ገለልተኛ ሀኖ የጻፈው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ መጽሀፍ ቅዱስን፣ ሌሎች ቅዱሳን መጻህፍትን እና ታሪክን መርምሯል፡፡