ermias mesfin marked as Want to read
2024-08-20 12:19:49
Yonas Bojaa marked as I have read it
2024-08-15 09:16:23
TAMENE BELETE commented
2024-07-23 21:47:41
ከፍያለው ግን እንዴት ላውርድ
TAMENE BELETE commented
2024-07-23 21:46:39
Fb
Bekalu Melak marked as Currently Reading
2024-07-19 08:07:24
tabu deressa marked as Currently Reading
2024-07-08 06:36:15
Abebaw Desalegn marked as Currently Reading
2024-05-25 19:04:19
Abebaw Desalegn rated 5
2024-05-25 19:03:57
Abebaw Desalegn commented
2024-05-25 19:03:02
" የምንተዋወቅ አይመስለኝም። እኔ በበኩሌ ከዚህ በፊት እንደማላውቅሽ እርግጠኛ ነኝ ። '' አልኳት። '' እንዴት እርግጠኛ ሆንክ ? እኔ እንደውም የቅርብ ዘመድ ሁሉ የነበርን ይመስለኛል ።" አለች ነጭ ባርኔጣዋን እየነካካች ። አለባበሷ ምንም ምቾት አልሰጠኝም። ከርቀት ለሚያዬን ሰው የሆነ ነገር እንዲጠረጥር የሚያደርግ ዓይነት አለባበስ ነበር ። " የመጣሁበትን ጉዳይ ከጨረስን መሄድ እችላለሁ ?" በማለት ወደመጣሁበት አቅጣጫ መልከት አደረኩ ። " ጠንቋይ ቤት ሄደን ለምን አንተን ሳይህ የተለዬ ስሜት እንደተሰማኝ እንድንጠይቅ ነበር ያስጠራሁህ። " አለች። ይቺ ልጅ ትቀልዳለች ልበል ? ጠንቋዩ ፍቅር ይዞሻል እንዲላት ነው የፈለገቺው?
Abebaw Desalegn commented
2024-05-25 19:02:31
" ምንም " በማለት መለስኩላት ። በዚህን ግዜ ድንገት ካቀረቀርኩበት ቀና ብዬ ስለነበር ዓይን ለዓይን ተጋጨን። ለምን እንደሆነ ሳላውቅ ልቤ በድንጋጤ ስትመታ ይታወቀኛል። " የሆነ ቦታ የማውቅህ ይመስለኛል ። " አለች ዓይኖቿን ከ ዓይኖቼ ሳትነቅል። '' አይመስለኝም እመቤቴ " አልኳት ዓይኖቿን ላለማየት ዓይኖቼ እየሸሹ ። " አክብሮቱን ብትተወው ደስ ይለኛል ሔኖክ" አለቺኝ የውሸቷን እየተኮሳተረች። ይቺ ልጅ ምን እያደረገች ነው ? ንግስትም የውሸት ይኮሳተራል እንዴ ? '' ካዬሁህ ቀን ጀምሮ እንግዳ ስሜት እየተሰማኝ ነው ። ለዛም ከዚህ በፊት እንደምንተዋወቅ ዓይነት ስሜት የሚሰማኝ።" አለች። '' ስለምትወጂኝ ነው '' አልኳት ? እኔ እንጃ ያልኳትስ አልመሰለኝም። ምክንያቱም ፊቷ ላይ ምንም ዓይነት ስሜት አላነበብኩም ። ብያት ቢሆንስ ግን? ብላትስ ግን ?
Abebaw Desalegn commented
2024-05-25 19:01:28
ሔኖክ ኦክሲን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዬሗት ቤተመንግስቱ ውስጥ የተጋጨን ዕለት ነበር ። ገና እንዳየሗት ነበር የሆነ የማላውቀው ስሜት የተሰማኝ። የሆነ አለ አይደል ! ብቻ እንግዳ የሆነ ስሜት ። ብቻ ለመግለጽ የሚያስቸግር ዓይነት ስሜት እንበለው። ከዛች ቀን ጀምሮ ግራ ገብቶኛል ። ስለዛ እንግዳ ስሜት ማሰላሰል ማቆም አልቻልኩም ። የሆነ ቁርኝት በመካከላችን እንዳለ ዓይነት ነገር ይሰማኛል። ለምን እንደዚህ እንደሚሰማኝ አላውቅም። ይሔ ነው ብዬ ልገልፀው የማልችለው ዓይነት ስሜት ! ፍቅር ይዞኝ ይሆን እንዴ ? ኦ ! ያ በፍፁም ሊሆን አይችልም ። የሰው ሚስት ያውም የንጉሥ! ለማሰብ መከጀሉ በራሱ ሐጢያት ነው ። ኦክሲን ግን አለማሰብ አልቻልኩም ። በቤተመንግስቱ ውስጥ ስዘዋወር ድንገት ካገኘሗት ሳላስበው ፈገግ እላለሁ። እሷም መልሳ ፈገግ ትልልኛለች። አቤት ፈገግታዋ ሲያምር ። ከንጉሥ ሚስት ጋር በድብቅ ፈገግታ መለዋወጥ በራሱ የሆነ ዓይነት ሚስጥራዊ ስሜትን ይፈጥራል ። ሁልጊዜ በድብቅ አይቻት ፈገግ ስትልልኝ " ይቺ ልጅ ! " እላለሁ በሀሳቤ ።
Abebaw Desalegn commented
2024-05-25 19:00:31
" እና እንዴት ነው አልሚሪስን ወደ ሕያዋን ምድር መመለስ የሚቻለው ? " በማለት ጠየኩት ። " በጥንት ጊዜ ኢትዮጵያ በምትባል ሐገር ውስጥ አንድ አስፈሪ አኒሞን የሐገሬውን ዜጋ እየለቃቀመ ይበላ ጀመር ። ሐገሬውም በዚህ አውሬ እጅጉን ስለተማረረ ከንጉሱ ጋር ተስማምተው ቄሶችን ማማከር ጀመሩ። ቄሶቹም ነገሩ የአማልክት ቁጣ እንደሆነ ገለፁ። ቁጣውም የመጣው የንጉሱ ሚስት ልጄ ከአማልክት የበለጠች ቆንጆ ነች ብላ ጉራ በመንዛቷ መሆኑን ተናገሩ። የመጣው መቅሰፍትም የሚቆመው የንጉሱ ድንግል ሴት ልጅ ለአውሬው የተሰጠች እንደሆነ ተናገሩ። ይህንን ሲሰሙ ንግስቲቱና ንጉሱ አምርረው አዘኑ ። ይሁነንና ንጉሱ በመጨረሻም በቄሶቹ ሀሳብ ተስማማ ። ነገር ግን ንግስቲቱ እንዲህ ያለውን ሀሳብ እሺ ብላ የምትቀበል አልነበረችምና የመፍትሔ ሀሳብ ስታፈላልግ ምንም ነገር ስለማይሳናቸው የሚስጥራዊው ዓለም ጠባቂዎች ሰማች ። የሚስጥራዊውን ዓለም ጠባቂዎችንም እርዳታ ጠየቀች ። የሚስጥራዊው ዓለም ጠባቂዎች ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይወዱ ስለነበር ለእርዳታ ፈጥነው ደረሱ ። ውቢቷ ልዕልት ሳባ በአውሬው ከመሰልቀጧ በፊት ቀድመው ደርሰው አውሬውን በሰይፍ አረዱት ።አውሬው ሲሞት የፈሰሰው ደም የልዕልቷን ተረከዝ አግኝቶት ኖሮ ተረከዟ ወደ አህያ እግር ተቀየረ። በዚህም ልዕልቷ ምንም ያህል ቆንጆ ብትሆንም ስትራመድ ታነክስ ስለነበር የሚያያት ሁሉ ከንፈሩን ይመጥ ጀመር ። ይህቺ ልዕልት በሗላ በቤተሰቦቿ ዙፋን ተተክታ ንግስት ስትሆን ንጉስ ሰለሞንን ለመጎብኘት ወደ እስራኤል ተጉዋዘች። እግሯ የእስራኤልን ምድር እንደረገጠ ተረከዟ ላይ የነበረው የአህያ እግር ወለቀ ። ያንን የአህያ እግር አምጥታቹ በሙታንና በሕያዋን አገናኝ ድልድይ በሆነችው ታተይ ፊት አቃጥሉት ። ጭሱ በታተይ አፍንጫ ሲገባ ያኔ እንደበፊቱ ዛሮችና የዛር ውላጆች በሙታንና በሕያዋን መካከል መገኘት እንጀምራለን። አልሚሪስ ታምሪያ የሰጠችውን ክታብ ታተይ አጠገብ ጥሎት ነው ወደ ሙታን ዓለም የገባው ስለዚህ መንክር ክታቡን ይዞ ወደ ሙታን ዓለም በመግባት ለአልሚሪስ ሊሰጠው ይገባል ። ነገር ግን ይህንን ሁሉ ለማድረግ መጀመሪያ ንግስተ ሳባ ከሞት መነሳት አለባት ። ለዚህም ይሆን ዘንድ የሞቱ ሰዎችን ማስነሳት የሚችል ፍጡር መፈለግ አለባችሁ። " በማለት እንዴት አልሚሪስን ወደ ሕያዋን ምድር መመለስ እንደሚቻል አብራራልኝ።
Abebaw Desalegn commented
2024-05-25 19:00:02
ዕሙ ከጠፋች ሁለተኛ ቀኑን ያዘ ። እንደቀልድ ደብዛዋ ጠፋ ። ብንፈልግ ብናስፈልግ አየናት የሚል ጠፋ ። በአጋጣሚ መንገድ ላይ ከኦክሲ ጋር ስንገናኝ ፈገግ ትልልኛለች ። ፈገግታዋን ሲያይ ልቤ ጥፍት ይልላት ጀመር ። እንደው አንድ ቀን ሰው በሌለበት ባገኘሗት እል ጀመር ። ምን እንደነካኝ እንጃ ሁለመናዬ ኦክሲን ኦክሲን ይለኛል ። ስለሷ ሳስብ ልቤ አከባቢ ይነዝረኛል ። የኔ ውድ ኦክሲ የደም ዝውውሬን ሁላ ተቆጣጥራዋለች ። የምር ይሔን ያልኩት እኔ ነኝ !? ምን ሆኜ ነው ግን ? የንጉሥ ሚስትን መመኘት ታላቅ ድፍረት ቢሆንም እኔ ግን ከመመኘት አልፎ ለመቃመስ አቀድኩ ። ይሔ ደግሞ በራስ ላይ ሞት እንደመፍረድ ነው ። ከተጋደምኩበት እንደምንም እየተንጠራራሁ ተነሳሁ ። ቀኑን ሙሉ በማላውቀው ምክንያት ደብሮኝ ተኝቼ ነው የዋልኩት። ጫማዬን ተጫምቼ ወደ በሩ አመራሁ። እየመሸ ስለነበር ድንግዝግዝ ያለ ብርሀን ነው የሚታየኝ ። በሩን ከፍቼ ወጣሁ ። ቤተ መንግስቱ ያለወትሮው ፀጥታ ሰፍኖታል ። ሽርጉድ የሚያበዙትን ሰራተኞችን እንኳን ዛሬ ላያቸው አልቻልኹም ። ድንገት ከኮሪደሩ ጫፍ ላይ የሆነ ሰው ብቅ አለ። ከርቀት መለየት የቻልኩት ነጭ ልብስ እንደለበሰ ብቻ ነው ። ትንሽ ቆይቶ ያው ሰው ቀኝ እጁን አንስቶ አውለበለበልኝ ። የሰውዬውን አቅጣጫ ተከትዬ መራመድ ጀመርኩ ። ወደሰውዬው እየቀረብኩ ስመጣ ቀሚስ የለበሰች ሴት መሆኗን እየለየሁ መጣሁ። አዎን ኦክሲ ናት ። የኔ ኦክሲ ፊቷ ላይ የሆነ ነገር እንዳማራት ይናገራል ። ደሞ ያንን ፈገግታዋን አብርታዋለች ። ቀስ እያልኩ ወዳለችበት ተጠጋሁ ። ድንግዝግዝ ባለው ብርሀንም ቢሆን ውበቷን ለማስተዋል አይከብድም ። አጠገቧ ልደርስ ስል እጥፍ አለችና ከዓይኔ ተሰወረች ። ምንድነው ጉዱ ? በህልሜ ነው እንዴ !? ህልም ከሆነ እንድነቃ በማሰብ ሀሳቤን ሰብስቤ ትኩረቴን ንቃት ላይ አደረኩ ። ግን ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ። ያለወትሮው የቤተ መንግስቱ መብራት አለመብራቱ እንግዳ ስሜት ፈጠረብኝ ። በቁም እየቃዠሁ ነው ? ተራመድኩና ኦክሲ ወደታጠፈችበት አቅጣጫ ተመለከትኩ ። መታጠፊያው አጠገብ ግድግዳውን ታካ ቆማለች ። የምሽቱ ንፋስ ፀጉሯን እያዘናፈለ ያጫውተው ጀምሯል ። ከንፈሯን በምላሷ እያረጠበች በስስት ተመለከተችኝ ።
Negese Dereje marked as Currently Reading
2024-05-19 17:15:42
Deribe Zewde commented
2024-04-19 06:49:32
I want to read it
Deribe Zewde marked as Want to read
2024-04-19 06:48:46